የኢትዮጵያ ወጣት ዕጣ፡ ከሞት ሽሽቶ ወደ ሞት!


 “ልጄ ትሞትብኛህ፣ ጊዜው እሰኪያልፍ አዲስ አበባ ሄደህ ተደበቅልኝ” ይህ አንድት ኢትዮጵያዊት እናት ልጇን ከሞት ለማሸሽ እንባ እየተናነቃት የተናገረችው ቃል ነው፡፡ ይህን ቃል ከእናቱ አንደበት የሰማው ወጣት ደግሞ ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ ወደ ትውልድ ቀዬው የተመለሰ ነው፡፡

አንድ ወጣት የናፈቁትን ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ ከመቀሌ ወደ ትውልድ አካባቢው ደብብ ትግራይ ይጓዛል፡፡ ወጣቱን በጉዞ ላይ እያለ እናቱ እንዴት በደስታ አቅፋ እንደምትቀበለው እያሰበ ምን በደርስኩ ብሎ ልቡ ቀድሞ ካደገበት ቀዬ ደርሷል፡፡

የጠበቀው ያ ማየት የጠበቀው የእናቱ በደስታ የፈካ ፊትና የስስት እቅፍ አይደለም፡፡ ወጣቱ ከሰባት ወራት በኋላ ወደ ትውልድ መንደሩ ሲደርስ እንደጠበቀው እናቱ በደስታ አቅፋ እንድትቀበለው እየጠበቀ ቢሆንም፣ ያልተለመደና ያልጠበቀው ነገር ይገጥመዋል፡፡

ወጣቱ ከናፈቃት እናቱ ፊት ላይ በተያዩ ቅጽበት ያነበበው ምስል ከጠበቀው በተቃታኒ እጅግ የመከፋት ስሜት ሆነብት፡፡ ወጣቱ ያልጠበቀውን የእናቱን መከፋት ገና ሳያቅፋት እንደተመለከተ ወደ አእምሮው የመጣው አንድ በጎ ያልሆነ መርዶ እንደሚነገረው ነው፡፡

በናፈቃት እናቱ የተከፋ ፊት አቀባብል የተደረገለት ወጣቱ የመጀመሪያ ጥያቄው “እናቴ አለፈች?” የሚል ነበር፡፡ እናቱ የተከፋ ፊቷን በፈገግታ ለመሸፈን እየቃጣት ለልጇ ጥያቄ መልስ ሳትሰጥ “ልጄ ምነው አሁን መጣህብኝ?” በማለት የራሷን ጥያቄ አስከትላ አይን አይኑን አትኩራ ተመለከተች፡፡

ልጅ ባልጠበቀው ሁኔታ ግራ ተጋብቶ የአያቱን መሞት እንደሚረዳ እየጠበቀ እናቱ ወደቤት ይዛው ገብታ እንዴት እንደሰነበተ በመጠየቅ ቡና መቁላት ጀመረች፡፡ እናት ቡናዋን እየቆላች ወደ ተረጋጋ የናፍቆት ጭውውት መግባቷን የታበው ልጅ፣ “ለምን መጣህብኝ” መባሉ እያሰ በማውጣት በማውረድ አእምሮው ምላሽ ፍልጋ እየባዘ ነው፡፡

ወጣቱ በተደጋጋሚ ስልክ እየደወለች መናፈቋን በመግለጽ እንድጠይቃት ከምትጠይቀው እናቱ ያልጠበቀው ነገር ስለገጠመው ቢደነግጥም፣ ለምን መጣህብኝ ማለቷ አልተገለጸለትም፡፡ የተነፋፈቁ እናት እና ልጅ በቅጽበት በፍቅር መተቃቀፍ ሲገባቸው በግራ መጋባትና ሰሜት የተፋጠጡት እናት በአእምሮዋ ላይ ልጇን እንደሚነጥቃት በተሳለባት ጦርነት ነው፡፡

እናት ለወትሮው እንድጠይቃት ስትወተውተው የነበረው ልጇ ቀን ቆርጦ ከፊቷ ሲደርስ በጭንቀት የተቀበለችው፣ በአእምሮዋ የሞያቃጭለውን ጦርነት በማሰብ ነው፡፡ ልጅ የእናቱን የጭንቀት ስሜት ለማረሳሳት ከሰፈር ልጆች ጋር ለመጫወት ወደ ቀዬው ጎራ ቢልም፣ እናት ብዙም ሳትቆይተ ተከትላ ሂድልኝ ማለቷን ቀጥላለች፡፡

እናልት ልጇን ጨዋታ ከደራበት ለይታ “በርግጥ የምትወደኝ ከሆነ፣ አድምጠኝ። በሮቹን ሸጠን ገንዘብ እንሰጥሃለን። ወደ አዲስ አበባ ሂድ፤ ነገሩ እስኪቀየር ድረስ አትመለስ” አለችው፡፡ እናት አስከትላ “እንድትሞትብኝ አልፈልግም” በማለት ወደ ለጦርነት በግዳጅ ከመያዙ በፊት እንዲያመልጥ አጥብቃ ተጠይቀዋለች፡፡

ልጅም ከዚህ ቀደም በነበረው የኹለት ዓመቱን ደም አፋሳሽ የእርስ በእርስ ጦርነት የጓደኞቹን ህይወት ከመብላት የዘዘለለ ውጤት እንዳላመጣ ያመናል፡፡ እም ከእናቱ የቀረበለትን ከሚመጣው ጦርነት የመሸሽ አማራጭ ተቀብሎ፣ አሁን ላይ በህወሓት የሚደረገውን የጦርነት ድግስ እንደማይካፈል ይገልጻል፡፡

ለዚህም የሚያቀርበው ምክንያት ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት የሚያሳምንት ምክንያት ስለነበረ እንደሌሎች ጓደኞቼ ሁሉ ታግያለሁ ይላል፡፡ አንድያ ህወይቱን አስይዞ በጦርነቱ የታተፈው ለቤሰተብ፣ ከሕዝብና ለመሬት እንጂ ለህወሓት እንዳልነበር ይገልጻል፡፡

በወቅቱ ፍትሐዊ ምክንያት እንዳለ ስለሚያምን እንደሌሎች ባለደረቦቹ ለመሞት ቆርጦ በጦርነቱ የተሳተፈ ቢሆንም፣ ዋጋ ከፈልኩለት የሚለው ተስፋ እንደ ጉም መትነኑን ይገልጻል፡፡ “አሁን ያ ሁሉ መስዋትነት የከፈልንለት ትግል ምንም” ሆኖ ቀርቷል የሚለው ወጣቱ፣ ዛሬ ላይ የህወሓት አመራሮች ለራሳቸው ስልጣን መደላደል ለትግራይ ወጣት ዳግም ጦርነት እየደገሱ ነው ይላል፡፡

የህወሓት አመራሮች ያን ሁሉ ወጣት በጦርነት ያስጨረሱት በራሳቸው ጥቅም ስሌት መሆኑን ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ብዙዎች መገንዘባቸውን እየገለጹ ነው፡፡ ህወሓት እና የፌደራል መንግሥቱ ለዳግም ጦርነት ውረድ እንውረድ መባባላቸው ከጀመሩ የሰነባበቱ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ውጥረቱ አይሎ ጦርነቱ ከዛሬ ነገ ፈነዳ እየተባለ እየተጠበቀ ነው፡፡

የትግራይ እናትም ተረፋትን ልጇን ለጦርነት ላለመገበር ወደ ማኸል አገር እንዲሸሸግላት ያላትን አመጣ ሰጥታ እሸኘች ነው፡፡ ጊዜው እስከሚያልፍ በማኸል አገር ተደብቀው እንዲቆዩ በእናታቸው አደራ የተሰጣቸው የትግይ ወጣቶች ከመቀሌ የወጣው እግራቸው አዲስ አበባ ላይ አያርፍም፡፡

ለመሸሸጊያ በተመረጠችው አዲስ አበባ ብዙም ውለው ሳያደሩ ከያሉት ተጠራርተው ከፊት ለፊታቸው ሞት እንደተደቀነ እያወቁ የባህር ስደትን ይመርጣሉ፡፡ ያላትን ጥሪት አማጣ ልጇን ከጦርነት የደበቀች የመሰላት እናትም ብዙም ሳይቆይ የእገታ ወይም የሞት መርዶ ትሰማለች፡፡

የትግራይ ወጣቶች የሀገራቸውን ሞት ሸሽተው “የየመን ባህር ይብላን ብለው” በአስር ሺዎች እየተጠራሩ ቀን በቀን ወደ ሞት እየተመሙ ነው፡፡ እንዳሉትም በሀገራቸው ተስፋ ቆርጠው የመረጡት ስደት በልማደኛው የየመን ባህር ላይ ግብረኛ መሆናቸውን፣ የሰሞነኛው 142 ወጣቶች ሞት የማረጋገጫ ነው፡፡

ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ወጣት በአሁኑ ወቅር ተስፋ በማጣት በአራቱም ማዕዘን ስደትን ምርጫው ያደረገ ቢሆንም፣ የትግራይ እጅግ የከፋ ሆኗል፡፡ የትግራይ ወጣቶች  ስደት የድህረ ግጭት ቀውስ ያጎሳቆላቸው ሳያንስ፣ የህወሓት መሪዎች ዳግም ጦርነት ሲደግሱላቸው ቆመው ከመመልከት እየተሰደዱ መሞትን መርጠዋል፡፡

ምንም እንኳን በራስ ወገን ሥልጣን ጥመኞች የጦርነት ድግስ ላለመሳተፍ ወጣቱ አቋም ቢይዝም፣ የሀገሩን ሞት ሸሽቶ ራሱን ለየመን ባህር አሳልፎ ተገቢ አለመሆኑን ብዙዎች ይገልጻሉ፡፡ ወጣቱ ከሞት ሸሽቶ ወደ ሞት ከመትመም ይልቅ የቀውስ አዙሪት አስኳል የሆኑትን አካላት ለይቶ መታገል የተሻለ መንገድ መሆኑን እምብዛም አጠራጣሪ አይደለም፡፡

የትግራይ ወጣት እየረገመው የሚገኘውን ህወሓትን ለመታገልም አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን በኒው ሁማኒታሪያን ላይ የተሰራቸው ወጣት ታሪክ ያስረዳል፡፡ በአሁኑ ወቅት ህወሓትን የተቃወሙ ወጣቶች በሁለት መስመር የተሰለፉ ሲሆን፣ በአንድ በኩል አላይም አልሰማም ብሎ መሰደድ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለአልሞት ባይ ተጋዳይነት ጫካ መግባት ነው፡፡

ህወሓት ለትግራይ ህዝብ ተጨማሪ የጦርነት ጦስ እያመጣ ነው ያሉ ወጣቶች ወደ ትጥቅ ትግል መግባታቸው ይነገራል፡፡ ራሳቸውን “ሓራ መሬት” ወይም የትግራይ ሰላም ኃይል ብለው የሚጠሩ የታጠቁ ኃይሎች ህወሓት ለመታገል በሚል በአፋር ክልል መደራጀት ከጀመሩ ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡

የተወሰኑ ወጣቶች ህወሓትን ለማታገል ጨከነው ጫካ ቢገቡም፣ የትግራይ ሰራዊት ወይም ቲዲኤፍ ተብሎ በካምፕ የተጠረነፈው ወጣት ደግሞ ለዳግም ጦርነት ትዕዛዝ እየተጠባበቀ ነው፡፡ ህወሓት በሚመራው እና በተገንጣዩ ሓራ መሬት መካከል የእርስ በእርስ ግጭቱ የተጀመረ ሲሆን፣ በቅርቡ ተኩስ ገጥመው እንደበር ይታወሳል፡፡

በዚህ ማኸል “ወንድም ወንድሙን” በሚገድልበት የትግራይ እርስ በእርስ ግጭት ህወይታችንን አንገብርም ያሉ ወጣቶች፣ ህወይታቸውን አስይዘው ስደትን መርጠዋል፡፡ በሌላ በኩል ከሁለት ጎራ ተሰልፎ እርስ በእርስ ከመዋጋቱ የለሁበትም ያለው ወጣት በሰላማዊ መንገድ “ጦርነት በቃን” የሚል ድምጽ እያሰማ ነው፡፡

ከሰሞኑ በትግራይ ወጣቶች ዘንድ “ጦርነት አንፈልግም” የሚል ድምጽ በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት እየተሰራጨ ነው፡፡ “ጦርነት በቃን” የሚለው ድምጽ በዋናነት ከትግራይ ወጣቶች በኩል ጎልቶ የተሰማው፣ ትግራይ ከተለያየ አቅጣጫ የጦርነት ቀጠና የመሆን ስጋት ተደቅኖባታል በሚል ነው፡፡

ትግራይ በአሁኑ ወቅት በራሷ ኃይሎች የእርስ በእርስ ግጭት፣ የህወሓት እና ፌደራል መንግሥት ወረድ እንውረድ ፉከራ፣ እንዲሁም በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት አጣብቂኝ ውስጥ ገብታለች፡፡ ሦስቱም የጦርነት ጎራዎች በራሳቸው የቆሙ አለመሆናቸው ደግሞ ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡

የትግራይ ኃይሎች የእርስ በእርስ ግጭትም ይሁን የህወሓት እና የፌደራል መንግሥቱ፣ እንዲሁም የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ውጥረት በረዥም ሰንሰለት የተሳሰሩ ናቸው፡፡ አንዱ ለይቶለት ከፈነዳ እጅግ አሳሳቢ ቀውስ የሚያስከትል ቀጠናዊ ጦርነት መቀጣጠሉ አይቀሬ መሆኑን የዘረፉ አዋቂዎች ይገልጻሉ፡፡

በህወሓት እና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ጦርነት ቢቀሰቀስ፣ ሓራ መሬት እና ኤርትራ በየፊናቸው መደረባቸው አይቀሬ መሆኑ ከወዲሁ እየታየ ነው፡፡ በእነ ጌታቸው ረዳ እንደሚደገፍ የሚነገርለት ሓራ መሬት የፌደራል መንግሥቱ አጋር ሲሆን፣ ኤርትራ ደግሞ ህወሓት አጋርነቷን በግልጽ እያሳየች ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት በአራቱም ማዕዘን ያለ ወጣት አፍላነት ዕድሜን እየበላ ያለውን የእርስ በእርስ ጦርነት ባይደግፍም የሚያስቆምበት አቅም አለው የሚለው ጉዳይ በራሱ ጥያቄ ነው፡፡ ምንም እንኳን ወጣቱም ይሁን እንደ ህዝብ የጦርነት ድጋፍ ዝንባሌ ባይኖርም፣ የጦርነት በቃችሁ ለማለት በአንድነት የመቆም ችግር ይታያል፡፡

በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የቀጠለውን ጦርነት ለማስቆምም ይሁን የሚመጣውን ለማስቀረት ሕዝብ የተባበረ አቅሙን ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ያ አንዱ ቤት የሚነደው እሳት እኔ ጋር አይደረስም ብሎ ማዶ ለማዶ መተያየት መጨረሻው አብሮ መጥፋትን እንጂ፣ ለማንኛውም አካል ስኬት አይስከገኝም፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ!!


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የአብይ አህመድ እና ኢሳያስ አፈወርቂ መዋጊያዎች!

ኢትዮጵያን ማን ያሻግራት?

ዳግማዊ ትግራይ በአማራ ላይ!