ልጥፎች

ከጃንዋሪ, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዶናልድ ትራምፕ በአባይ ጉዳይ ዛሬም የካይሮ ጠበቃ ሆነው ተከስተዋል

ምስል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው ያልተሳካላቸውን የእጅ ጥምዘዛ ካርድ ጊዜ ጠብቀው መዘውታል። ትራምፕ ተቋርጦ የቆየውን የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር ለማስጀመር፣ ለግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በጻፉት ደብዳቤ ፍላጓታቸውን ገልጸዋል። ትራምፕ በመጀመሪያ ዙር የሥልጣን ዘመናቸው በቀጥታ ወደ ነጩ ቤተመንግሥት ተጎትተው ባስገቡት ድርድር፣ ያጡትን ውጤት በሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸው ለማሳካት በድጋሚ ካርድ መዘዋል። በመጀመሪያ ዙር የአደራዳሪነት ሚናቸው ለግብፅ ውግንና በማሳየት 'ግድቡን ታፈነዳዋለች' በሚለው ንግግራቸው የሚታወቁት ትራምፕ፣ ዛሬም ለካይሮ ያላቸውን ውግንና በደብዳቤያቸው አንጸባርቀዋል። ትራምፕ ለግብፁ ፕሬዜዳንት በጻፉት ደብዳቤ   "ባለን የግል ወዳጅነት መንፈስ እና አሜሪካ ለግብፅ ሕዝብ ሰላም እና ደኅንነት ባላት ቁርጠኝነት፣ በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን 'የአባይን ውሃ መጋራት' ጥያቄ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በኃላፊነት መንፈስ ለመፍታት አደራዳሪነቷን ዳግም ለመጀመር ዝግጁ ነኝ " ብለዋል። አክለውም "በቀጠና የትኛውም አገር የአባይን ውድ ሃብት በተናጠል መቆጣጠር እና በሂደቱ ጎረቤቶቹን መበደል የለበትም" በማለት፣ ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ጫና የመፍጠር በተደጋጋሚ የምትንጸባርቀውን አቋም ተጋርተዋል። ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባጋሩት በዚህ ደብዳቤ ላይ "ቡድኔ እና እኔ የአባይ ወንዝ ለግብፅ እና ለሕዝቧ ያለውን ጥቅም እንረዳለን" ብለዋል። ይህ የትራምፕ አድሎ የተጫነው አቋም አስጀምረዋለሁ በሚሉት ድርድር ላይ በግልፅ እንደሚንጸባረቅ ከወዲሁ አመላካች ሆኗል። ትራምፕ በደብዳቤያቸው ላይ ...