ልጥፎች

ከኦገስት, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የኢትዮጵያ ወጣት ዕጣ፡ ከሞት ሽሽቶ ወደ ሞት!

ምስል
  “ልጄ ትሞትብኛህ፣ ጊዜው እሰኪያልፍ አዲስ አበባ ሄደህ ተደበቅልኝ” ይህ አንድት ኢትዮጵያዊት እናት ልጇን ከሞት ለማሸሽ እንባ እየተናነቃት የተናገረችው ቃል ነው፡፡ ይህን ቃል ከእናቱ አንደበት የሰማው ወጣት ደግሞ ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ ወደ ትውልድ ቀዬው የተመለሰ ነው፡፡ አንድ ወጣት የናፈቁትን ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ ከመቀሌ ወደ ትውልድ አካባቢው ደብብ ትግራይ ይጓዛል፡፡ ወጣቱን በጉዞ ላይ እያለ እናቱ እንዴት በደስታ አቅፋ እንደምትቀበለው እያሰበ ምን በደርስኩ ብሎ ልቡ ቀድሞ ካደገበት ቀዬ ደርሷል፡፡ የጠበቀው ያ ማየት የጠበቀው የእናቱ በደስታ የፈካ ፊትና የስስት እቅፍ አይደለም፡፡ ወጣቱ ከሰባት ወራት በኋላ ወደ ትውልድ መንደሩ ሲደርስ እንደጠበቀው እናቱ በደስታ አቅፋ እንድትቀበለው እየጠበቀ ቢሆንም፣ ያልተለመደና ያልጠበቀው ነገር ይገጥመዋል፡፡ ወጣቱ ከናፈቃት እናቱ ፊት ላይ በተያዩ ቅጽበት ያነበበው ምስል ከጠበቀው በተቃታኒ እጅግ የመከፋት ስሜት ሆነብት፡፡ ወጣቱ ያልጠበቀውን የእናቱን መከፋት ገና ሳያቅፋት እንደተመለከተ ወደ አእምሮው የመጣው አንድ በጎ ያልሆነ መርዶ እንደሚነገረው ነው፡፡ በናፈቃት እናቱ የተከፋ ፊት አቀባብል የተደረገለት ወጣቱ የመጀመሪያ ጥያቄው “እናቴ አለፈች?” የሚል ነበር፡፡ እናቱ የተከፋ ፊቷን በፈገግታ ለመሸፈን እየቃጣት ለልጇ ጥያቄ መልስ ሳትሰጥ “ልጄ ምነው አሁን መጣህብኝ?” በማለት የራሷን ጥያቄ አስከትላ አይን አይኑን አትኩራ ተመለከተች፡፡ ልጅ ባልጠበቀው ሁኔታ ግራ ተጋብቶ የአያቱን መሞት እንደሚረዳ እየጠበቀ እናቱ ወደቤት ይዛው ገብታ እንዴት እንደሰነበተ በመጠየቅ ቡና መቁላት ጀመረች፡፡ እናት ቡናዋን እየቆላች ወደ ተረጋጋ የናፍቆት ጭውውት መግባቷን የታበው ልጅ፣ “ለምን መጣህብኝ” መባሉ እያሰ በማውጣት በማውረድ አእ...