ልጥፎች

ከዲሴምበር, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአብይ አህመድ እና ኢሳያስ አፈወርቂ መዋጊያዎች!

ምስል
ፋኖ፣ ኦነግ ሸኔና ብርጌድ   ንሓመዶም  ምንና ምን ናቸው? ዕለቱ መጋቢት 24 /2010 ዓ.ም ነው፡፡ ወቅቱም ኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫ በፖለቲካ ውጥንቅጥ የተወጠረችበት፡፡ በዚህ ውጥረት “ከሰማይ የወረደው ሙሴ” የተባለላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መሪ ሆነው ብቅ አሉ፡፡ ዕለቱ ኢትዮጵያዊነት፣ ሰላምና ፍቅር አየር ተሞላ፡፡ ኢትዮጵያዊያንም በፌስታ ፈነደቁና ተሰፋም አደረጉ፡፡ እነ ኦነግና ግንቦት ሰባትን ያቀፈችውን ኤርትራም የሰላም ጥሪ ቀረበላት፣ ተቀበለችም፣ ታጣቂዎቹም አገር አማን ብለው ወደ አገራቸው ገቡ፡፡ እነሆ እንዲህ አንዲህ እያሉ ወራት ዓመታትንን እየወለዱ፣ የኢትዮጵያዊነት ሸንገላ ቃላቶች በአየር ላይ እየከሰሙ፣ የተወጠረው   የፍቅር ፌሽታ በአቅጣጫው እየኮሰመነ፣ ታጣቂዎችም ተከዳን ብለው ጦራቸውን ወደ መንግሥት ካዞሩ ሰነባበቱ፡፡ በጣት ቀለበት የታሰረው የኢሳያስና የአብይም ወዳጅነት እነሆ እንዳልነበረ ሆኖ ጦር መማዘዝ ብቻ ቆርቷቸዋል፡፡ ሁለቱ መሪዎች በአንድ መድረክ ላይ ቆመው ማንም አይለየንም እንዳላሉ፣ በጎሪጥ መተያየት ጀምረዋል፡፡ ነገሮች እንዳልነበር ሆነው ተከረባብተው ጠላት ያሉትን ኃይል ለመውጋት በጋራ የተሰለፉ አካላት በየፊናቸው ጎራቸውን ለይተው አዲስ ጥምረት ለመመስረት እየጠሯሯጡ ነው፡፡ አብይና ኢሳያስ ሲለያዩ በታጠቁ ኃይሎች በኩል ለመወጋጋት ጉድጓድ እየማሱ ነው የሚለው ወሬ አየሩን ሞልቶት ሰንብቷል፡፡ ነገሩ በወሬ ብቻ የሚቆም አለመሆኑን ከሁለቱም አገራት በኩል ምልክቶች ታይተዋል፡፡ አብይና ኢሳያስ ለጎንዮሽ ውጋት የሚመዙት ካርድ እንደማይቸገሩ ለማሳየት ጥረት እያደረጉ ነው፡፡   ኦነግ ሸኔ በድርድር፣ ፋኖን በሰፈር ሽምግልና ለመደለል ጥረት ያደረገው መንግሥት እጅ ሲያጥረው፣ የእ...