ልጥፎች

ከሴፕቴምበር, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ኢትዮጵያን ማን ያሻግራት?

ምስል
  ኢትዮጵያን ማን ያሻግራት?   በጋዜጠኛ መርሻ ጥሩነህ በግራ በቀኝ ወጀብ በበዛበት ሁኔታ ቀናት ወራትን፣ ወራት ዓመታትን እየወለዱ ጊዜ ው  እየነጎደ ነው፡፡  ዓመቱ እጅግ ፈታኝ ዓመት ሆኖ ብቻ አላለፈም፣ ይልቁንም ለተተኪው ዓመት አዳሪ ችግሮችን አሸግሯል፡፡ በዚህ መሰል ወጀብ ውስጥ እያለፈች የምትገ ኘ ውን ኢትዮጵያ አሸጋሪ ትሻለች፡፡ ኢትዮጵያ ፈታኝ ወቅት ላይ እንደምትገኝ አሁን ላይ የገጠሟች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ መሆኑን፣ ከኃይማኖት ተቋማት እስከ፣ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እስከ ፖለቲካ አዋቂዎች፣ ከማኅበረሰብ አንቂ እስከ ተርታው ማኅበረሰብ በየፊናቸው ያረጋገጡት ሀቅ ነው፡፡ ጥያቄው ኢትዮጵያን ማን ያሸግራት? የሚለው ነው፡፡ በተከታወዩ ጽሑፍ የ2015 አብይት ጉዳዮች ምን እንደነበሩና ኢትዮጵያን ማን ያሻግራት የሚሉትን ጉዳዮችን በወፍ በረር እንመለከታለን፡፡ የ2015 አበይት ጉዳዮች ምን ነበሩ? የተጠናቀቀው 2015 እንዴ አገር ለኢትዮጵያ፣ እንዴ ዜጋ ለኢትዮጵያን በብዙ ችግሮች ታጅቦ ያለፈ ዓመት እንደነበር፣ በዓመቱ የተከናወኑ የፖለቲካ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አበይት ጉዳዮች አመለካች ናቸው፡፡ ü   የሰሜኑ ጦርነት ማብቃት የሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦርነት በፕሪቶሪያው የሰላም ምምነት መሰረት ከሁለት ዓመት ደም አፋሳሽ የእርስ በእርስ ጦርነት በኋላ ያበቃው፣ በተሸኘው 2015 ሁለተኛ ወር ላይ ነበር፡፡ ጥቅምት 23/2015 የፌዴራል መንግሥት እና ህወሓት በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ጦርነቱን ለማቆም የተስማሙበት ዓመት ሆኖ አልፏል፡፡ ይሁን እንጂ በሰላም ስምምነቱ መሰረት ይፈጸማሉ በተባሉ ጉዳዮች ላይ አሁንም ውዝግበቶ መነሳታቸውን ቀጥለዋል፡፡ የሚነሱ...