ልጥፎች

ከኦገስት, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዳግማዊ ትግራይ በአማራ ላይ!

ምስል
ዳግማዊ ትግራይ በአማራ ላይ! በጋዜጠኛ መርሻ ጥሩነህ ከሚሊዮን ዜጎች እልቂት እስከ ሚሊዮች አርዛት፣ ከሚሊዮኖች መፈናቀልና ጉስቁልና እስከ ትሪሊዮን ብር ውድመት ያስከተለው፣ የትግራይ እርስ በእርስ ጦርነት ዛሬም በሌላ ተረኛ ሕዝብ ላይ ተደቅኗል የሚሉ ድምጾ ከሰሞኑ ከየአቅጣጫው በስፋት ተሰምተዋል፡፡ የእነዚህ ድምጾች መነሻ ከትግራዩ ጦርነት ማብቃት ማግስት በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቀዎች እና በመንግሥት በካከል የተቀሰቀሰው ግጭት በሰላማዊ መንገድ ይፈታል ተብሎ ሲታሰብ ወደለየለት ውጊያ መሸጋገሩር ነው፡፡ በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት ከዚህ ደቀም ትግራይ ክልል የሆነውን የሚደግም አካሄዶችን በግልጽ እያሳየ ነው። የአማራ ክልሉ የጸጥታ ችግር በትግራይ ጦርነት ወቅት የተፈጸሙ ተፊ ጥቃቶችና ጥፋቶች ሊስከተል እንደሚችል፣ አደባባይ የወጡ ማስረጃዎች ከወዲሁ ፍንትው ብለው እየታዩ ነው፡፡ በትግራዩ ጦርነት ጅማሮ ላይ የታዩ ፍረጃዎች፣ የክልል መንግሥታት የጦርነት ድጋፍ ዘመቻ፣ የእነ ዳቆን ዳንኤል ክብረትና መሰሎቹ የተለመደ ጦርነት የማቀጣጠል ተግባር፣ በከተሞች ጭምር የሚፈጸሙ ድሮን ጥቃቶች፣ የሰላማዊ ሰዎች ግድያ፣ አማራ ተወላጆች ጅመላ እስር፣ በፌዴራል መንግሥቱ በኩል በግልጽ ተጀምሯል። ያኔ በትግራዩ ጦርነት ዋዜማ ከመቀሌ አዲስ አበባ፣ ከአዲስ አበባ መቀሌ በብልጽግና እና በሕወሓት መካከል ሲዥጎደጎዱ የነበሩ የቃላት ጦርነቶችና እርስ በእርስ መፈራረጆች፣ ዛሬም በመንግሥት እና በአማራ ክልል በመንግሥት ላይ ባመጹ ኃይሎች መካከል በግልጽ ተጀምሯል፡፡ የዛሬን አያድርገው እና ያኔ በለውጡ ሰሞን ሕወሓት ከአዲስ አበባ ተነቅሎ፣ መቀሌ ሲመሽግ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና መሰሎቻቸውን የፍረጃ ቃላት ተቀብለው በአደባባይ ሲያስተጋቡ የነበሩ የገዥው ብል...